Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ዕዝና ፌደራል ፖሊስ የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ታስቦ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ዕዝ እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በህወሓት የተፈጸመው የክህደት ጥቃት 2ኛ ዓመት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተዘክሯል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ እና በፌደራል ተቋማት ጥበቃ ላይ በነበሩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂና አስነዋሪ ጭፍጨፋ 2ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች አስበዋል፡፡

የመታሰቢያ መርሐ ግብሩ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ፣ ቀኝ እጅን በግራ ደረት ላይ በማድረግ ፣ ሁሉም ሰልፈኛ በተጠንቀቅ ቆሞ “ስለኢትዮጵያ የከፈላችሁትን አንረሳም” የሚል መልዕክት በማስተላለፍ ተዘክሯል፡፡

ዕለቱ የተዘከረበት ዋነ ዓላማም ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት የከፈሉትን እና እየከፈሉ ላሉት የሕይወት መስዋዕትነት የከበረ ዋጋ በመስጠት ለላቀ ዝግጁነት ለማነሳሳት እንደሆነ ታውቋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የተፈፀመው ክህደት አሳዛኝ እንደሆነ መግለጻቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.