ጉባዔው ለሰላም ስምምነቱ መሳካት ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲተባበር ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለሰላም ስምምነቱ መሳካት ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲተባበር ጥሪ አቀረበ፡፡
ጉባዔው በደቡብ አፍሪካ በመንግስትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ÷ የሰላም ስምምነቱ አስፈላጊ በመሆኑ እንደግፈዋለን ሲል ገልጿል፡፡
የጉባዔው ጠቅላይ ፀሀፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ÷ ለሰላም ስምምነቱ መሳካት ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ፀሀፊው ÷በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የሰላም ስምምነቱን በሚመለከት የሚሰራጩ አላስፈላጊ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡
የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሰላም በኢትዮጵያ በዘላቂነት እንዲሰፍን ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ጠቅሰው ÷ በመጪው ጊዜያትም ጉባኤው በሀገር የሰላም ግንባታ ሂደትና በዜጎች አብሮነት በትጋት እንደሚሰራ ነው የገለጹት።
በአሸናፊ ሽብሩ እና ፍቅርተ ከበደ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!