የሀገር ውስጥ ዜና

ካናዳ የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነት ወሳኝ እርምጃ ነው አለች

By Meseret Awoke

November 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ካናዳ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ካናዳ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት እንደምታደንቅ ገልጸዋል፡፡

የተደረሰው የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነት ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ በሰላም ስምምነት ሂደቱ ውስጥ ለተሳተፉ ሌሎች አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሯ ÷ካናዳ የሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ነው ያረጋገጡት፡፡

ሁሉም ወገኖች የዜጎችን ደህንነት እንዲያረጋግጡና የኢትዮጵያን ህዝብ አንገብጋቢ የሰብዓዊ ፍላጎቶች እንዲፈቱም ጠይቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!