በመዲናዋ የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ከፊታችን ህዳር 1 ቀን ጀምሮ ይሰጣል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ከህዳር 1 ቀን 2015 ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚሰጥ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ላይ እያካሄደ ያለው ሪፎርም እንዲሳካ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ አቅጣጫ በተቀመጠበት መድረክ ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩ በመጪው ሳምንት ለሚጀመረው የመታወቂያ እድሳት በየደረጃው ያለው መዋቅር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አገልግሎት ፈላጊውን ህብረተሰብ በቀናነትና በቅልጥፍና ማስተናገድ እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።