Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ኅብረት ጉባዔ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ኅብረት የጋራ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡
በጋራ ጉባዔው ላይ÷ የአባል ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች፣ ቻንስለሮች ችና የልቀት የምርምር ተቋማት ዳይሬክተሮች እየተሳተፉ ነው፡፡
ጉባዔው ቅድሚያ ትኩረት በሰጠባቸው የምርምር አጀንዳዎችና በስልታዊ ዕቅዱ አፈጻጸም ላይ እየተወያየ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት ተልዕኮ÷ የአፍሪካ ተመራማሪዎችና የምርምር ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል ነው፡፡
በተጨማሪም በሚፈጥሩትና በሚያሰራጩት አዳዲስ የምርምር እውቀት የአፍሪካን ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ማገዝ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት አባላት የሆኑ 16 ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ዩኒቨርሲቲዎች በጉባዔው እየተሳተፉ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.