Fana: At a Speed of Life!

በውሃና ኢነርጂ ጉዳዮች ላይ ከኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃና ኢነርጂ ጉዳዮች ላይ ከኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ጋር በትብብር ለመሥራት በሚያስችለው ጉዳይ ላይ ተወያይቷል፡፡

ውይይቱን ያካሄዱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ እና የኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሳይመን ኦ ኮኔል ናቸው፡፡

ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ ባለፈው ዓመት በተካሄደ የሪፎርም ሥራ የመጠጥ ውሃ፣ የንፅሕና መጠበቂያ እና በኢነርጂ ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ አዳዲስ አደረጃጀቶች ተፈጥረው ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡

በተለይም በገጠሪቷ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተተግብረው በቀጥታ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ላይ ከኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት ጋር ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሠሩ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም እንደ ሀገር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ÷ የከርሰ ምድር ውሃ የማልማትና ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ፣ የዝናብ ውሃ የማሰባሰብና ጥቅም ላይ ማዋል፣ የውሃ መሠረተ ልማቶችና የውሃ ሐብት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ላይ በአጋርነት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

ሳይመን ኦ ኮኔል በበኩላቸው÷ በሞዛምቢክ፣ በኬኒያ እና ሌሎች ሀገራት ላይ ተሞክረው ውጤታማ በሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ፍላጎት አለን ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.