የሀገር ውስጥ ዜና

በሦስት ክልሎች ሰላምና ልማት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የተዘጋጀ የሰላም ጉባኤ እየተካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

November 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ሰላምና ልማት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት የተዘጋጀው የሰላም ጉባኤ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሐይማኖት አባቶችና በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረው የሰላም ጉባኤ÷ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

የኦሮሚያ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የጋራ የሰላምና የልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍሮምሳ ሰለሞን ባቀረቡት ጽሑፍ÷ የሦስቱም ክልሎች ሕዝቦች የረጅም ጊዜ ቁርኝት አላቸው ብለዋል፡፡

ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ የሦስቱን ክልሎች ሕዝቦች በሰላምና በልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የሕዝቦችን አብሮነትና ሰላም የሚያጠናክሩ እሴቶችን ለመጠበቅ በጋራ መሥራት ይገባል ማለታቸውንም የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!