Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለ15 የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለ15 የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች የድህረ ምረቃ ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠች፡፡

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከኢትዮጵያ መንግስት በተሰጠው የነፃ ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ለሚሆኑ ተማሪዎችን በትናንትናው ዕለት ሽኝት አድርጓል፡፡

የነጻ ትምህርት እድል ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግስት የደቡብ ሱዳንን የሰው ሀይል ልማትን ለማጠናከር እና የተቋማትን አቅም ግንባታ ለማሳደግ ካለው ቁርጠኝነት የተነሳ መሆኑ ተገልጿል።

በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ተማሪዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ወደ ሁለተኛ ቤታቸው እየሄዱ እንዳሉ ነግረዋቸዋል።

ዕድሉ በያዝነው ወር መጀመሪያ ወደ አዲስ አበባ ከተጓዙት ሃያ ዘጠኝ የደቡብ ሱዳን የህክምና ተማሪዎች በተጨማሪ የተሰጠ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.