ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡
በውይይቱ ላይ የሁለቱ ምክር ቤት አፈጉባኤዎች፣ ርዕሰ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬዲዋን ሁሴን በውይይቱ የተደረሰውን ስምምነት በተመለከተ አጠቃላይ ገለፃ መደረጉን ተናግረዋል ።
የሰላም ስምምነቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያስጠበቀና የሀገር ሉዓላዊነትን ያከበረ ነው ብለዋል።
የሰላም ስምምነቱ የባከኑ ጊዜያትን የሚክስና የተጉዱ አካባቢዎችን በመልሶ ግንባታ ለማስተካከል ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን በውይይቱ ላይ መነሳቱን ገልጸዋል ።
በጦርነቱ የተጎዳችው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የሰላም ስምምነቱ ጥቅሙ የሁሉሞ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
የስምምነቱ አተገባበር ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል፡፡