Fana: At a Speed of Life!

ከ398 ሺህ በላይ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲገቡ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ398 ሺህ በላይ የተለያዩ ግብርና ቴክኖሎጂዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ ወደ ሀገር እንዲገቡ መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ባለፉት ጊዜያት የፖሊሲና የአሰራር ማሻሻያዎችን ማድረጉን ነው ያስታወቀው፡፡

በዚህም በክረምት ብቻ ይመረት የነበረውን የተለመደ አሰራር በመቀየር በበጋ ወቅትም አርሶ አደሩ መስኖን ተጠቅሞ እንዲያመርት ለማስቻል ከአጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በመሆኑም አርሶ አደሩ በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚ እየሆነ ነው ነው የተባለው፡፡

ምርትና ምርታማነትን ለመጨመርም የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገቡ ባለ ሃብቶች እንዲበረታቱ ከቀረጥና ታክስ ነጻ በማድረግ ለግብርናው አጋዥ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል፡፡

በዚህም በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት ብቻ 10 የተለያየ የግብርና ቴክኖሎጂዎች እንደ ትራክተር ፣ ኮምባይነርና ሁለገብ መውቂያ፣ የውሃ ፓምፕ ከእነመለዋወጫው እና መሰል እቃዎች በጥቅሉ 398 ሺህ 627 ብዛት ያላቸው የግብርና ቴክኖሎጂዎች በ23 ባለሀብቶች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.