ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር እና ድሬዳዋ ድል ቀንቷቸዋል

By Feven Bishaw

November 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ድሬዳዋ ላይ በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል።

10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከባሕር ዳር ባደረጉት ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ባለ ድል ሆኗል።

በጨዋታው ባሕርዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ2 አሸንፏል፡፡

የማሸነፊያ ጎሎችን ተስፋዬ ታምራት፣ ፉዐድ ፈረጃ እና ሀብታሙ ታደሠ አስቆጥረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መድንን ጎል ደግሞ ብሩክ ሙሉጌታ እና ኪቲካ ጅማ በጭማሪ ሰዓት አስቆጥረዋል፡፡

ምሽት 1 ሰአት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ባለሜዳዎቹ ድሬዳዋ ከተማዎች ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግደዋል።

ጨዋታውን ድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 1 ሲያሸንፍ፥ አሳንቴ ጎድፍሬድ፣ ቢኒያም ጌታቸው እና ዮሴፍ ዮሐንስ የድል ጎሎች ባለቤት ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ቡናን ማስተዛዘኛ ጎል ደግሞ አንተነህ ተፈራ በጭማሪ ሰአት አስቆጥሯል።