Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው – ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ሲሉ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ተናገሩ፡፡

የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኢሉሴጉን ኦባሳንጆ ለኢዜአ እንደተናገሩት በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው የሰላም ስምምነት ግጭትን በማስቆም ለዘላቂ ሰላም መስፈን አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው፡፡

ስምምነቱም ችግሮችን በዘላቂነት በውይይት እንዲፈቱ የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም አካላት ለተፈጻሚነቱ በጥበብና ሀገር ወዳድነት ስሜት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ በኢፌዴሪ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል ሲካሔድ የቆየው ውይይት የኢትዮጵያ ሕዝቦችን የጋራ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ስምምነቱ በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችል ያስቀመጠ ሲሆን፣ የህወሓት ታጣቂዎችም ትጥቅ የሚፈቱ ይሆናል።

በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎት እንዲጀመርም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.