Fana: At a Speed of Life!

ኤፓክ ለ28 የአሜሪካ የሕግ አውጪ ምክር ቤት እጩዎች ይሁንታ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ” (ኤፓክ) በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ለ28 የሕግ አውጪ ምክር ቤት እጩዎች ይሁንታ መስጠቱን አስታወቀ።

በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው ምርጫ ዘንድሮ ለ23ኛ ጊዜ የፊታችን ማክሰኞ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።

ለአሜሪካ ሕግ አውጪ ምክር ቤት 435 መቀመጫዎችና ከአስፈጻሚው 100 መቀመጫዎች ውስጥ 34ቱ ወይም አንድ ሶስተኛው ለምርጫ ይቀርባሉ።

‘የአሜሪካ ኢትዮጵያውያን የፐብሊክ አፌርስ ኮሚቴ’ የተሰኘው የፖለቲካ ተግባር ኮሚቴ በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ብሔራዊ ቅስቀሳ በይፋ ማስጀመሩ የሚታወስ ነው።

የኤፓክ የቦርድ አባል አቶ ፍስሀ አዱኛ ኤፓክ ከተቋቋመበት ዓላማ አንዱ የኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እንዲሁም በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ መስራት እንደሆነ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ የፖለቲካ ተግባር ኮሚቴው ከሚመለከታቸው አጋሮቹ ጋር በመሆን አላማውን ያሳካሉ ያላቸውን እጩዎች የማነጋገርና የመለየት ስራ ማከናወኑን ተናግረዋል።

የልየታው ሂደት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴን ጨምሮ በኮንግረስና ሴኔት የሚገኙ ቁልፍ የሚባሉ ኮሚቴዎችን የያዙ ባለስልጣናትን ያማከለ እንደሆነም አመላክተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.