Fana: At a Speed of Life!

ባለሐብቶች በመዲናዋ የሚቀርቡ የቤት ጥያቄዎችን ለማቃለል የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግል ባለሐብቱ በተዘረጉት የቤት ልማት ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍ ተደራራቢ የቤት ጥያቄዎችን ለማቃለል የበኩሉን አስተዋፅዖ እንዲያበረከት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በሳኩር ሪል ስቴት የተገነቡ 116 ቤቶችን እንዲሁም በአልሳም ግሩፕ የተገነቡ 360 ቤቶች እና የንግድ ሱቆችን መመረቃቸውን አንስተዋል፡፡

ከንቲባዋ ÷ የከተማዋ ነዋሪዎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ የመንግስት ጥረት ብቻውን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣ እንደማይችልም ጠቁመዋል፡፡

ስለሆነም የግል ባለሐብቱ በተዘረጉት የተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍ ተደራራቢ የቤት ጥያቄዎችን ለማቃለል የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያበረከት ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዛሬ የተመረቁት ቤቶች በቦታ አጠቃቀም፣ በዘመናዊነት፣ በጥራት የከተማዋን ገፅታ በመቀየር፣ የአኗኗር ባሕልን በማሻሻል እንዲሁም በሥራ ዕድል ፈጠራ ሚናቸው የጎላ መሆኑንም አውስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.