Fana: At a Speed of Life!

በጨለንቆ ከተማ በእሳት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ጨለንቆ ከተማ በእሳት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ሃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ አደጋው በጨለንቆ ከተማ ለነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች ነዳጅ የሚሸጡ ግለሰብ ቤታቸው ውስጥ የለኮሱት ሻማ በሚሸጡት ነዳጅ ላይ ወድቆ እሳት በማስነሳቱ የተከሰተ ነው።

በእሳት አደጋው ሳቢያም የቤቱን ባለቤት ጨምሮ የ6 ዓመት የልጅ ልጃቸው እና የ8 ዓመት የጎረቤት ልጅ ህይወታቸው አልፏል።

አደጋውን ተከትሎ ከእንቅልፏ የነቃች የ12 ዓመት ታዳጊ ህይወት መትረፉንም ኮማንደር ስዩም ተናግረዋል።

ሁለት መኖሪያ ቤቶች በእሳት አደጋው ሙሉ ለሙሉ የወደሙ ሲሆን፥ እሳቱ ወደ ሌሎች መኖሪያ ቤቶች እንዳይዛመት የከተማዋ ነዋሪዎች ባደረጉት ጥረት መቆጣጠር ተችሏልም ነው ያሉት።

በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ በመኖሪያ ቤቶች በመሸጥ መሰል አደጋዎች እንዲፈጠሩ የሚያደርጉ ግለሰቦችም ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ኮማንደር ስዩም ደገፋ አሳስበዋል።

በበላይ ተስፋዬ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.