Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የኮሮና ቫይረስ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቀነስ ከባለሀብቶች ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)መንግስት የኮሮና ቫይርስ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚያደረሰውን ጫና ለመቀነስ ከባለሀብቶች ጋር ተባበሮ እንደሚሰራ አስታወቀ።
 
የገንዘብ ሚኒስቴር እና የባህል ሚኒስቴር አመራሮች በሆቴልና ቱሪዝም ስራ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር የኮሮና ቫይርስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ባለው ጥረት ዙሪያ ውይይት ተደረጉ፡፡
 
በውይይቱ ላይም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
በዚህ ወቅትም መንግስት በኮሮና ቫይርስ ምክንያት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚያደረሰውን ጫና ከግምት ውስጥ በማሰገባት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ ነው የተገለፀው።
 
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ አለም ሀገራት በከፍተኛ ሁኔታ ሰብዓዊ እና ኦኮኖሚያ ጉዳቶችን እያስከተለ የሚገኝ ሲሆን÷ ከዚህም ውስጥ የሆቴል ዘርፉ አንዱ ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.