ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድደር ኢትዮጵያ ዩጋንዳን አሸነፈች
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድደር ኢትዮጵያ ዩጋንዳን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
የኢትዮጵያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ከድር ዓሊ ጨዋታው በተጀመረ 60ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ምድቧን በ4 ነጥብ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።
ብሔራዊ ቡድኑ ለግማሽ ፍፃሜው ከደቡብ ሱዳን ጋር የፊታችን ማክሰኞ ጥቅምት 29 ቀን የሚጋጠም ይሆናል፡፡