Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ደረጃ  “የሌማት ትሩፋት” የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ደረጃ  “የሌማት ትሩፋት”  የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።

እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተማሪዎች ምገባ እና በቆሻሻ አወጋገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ እንድትሆን አስተዋፅኦ ለነበራቸው ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ  ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተግኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ስታሸንፍ የሚያሸንፈው አፍሪካ መሆኑን እንረዳለን ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ እንግዶቿን ሁሉ በክብር እጇን ዘርግታ የምትቀበል የፍቅር ከተማ ነች ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ለከተማዋ የተሰጠው ሽልማት ስንቅም፣ ትጥቅም፣ ብርታትም  ሆኖን የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ከብልፅግና ለማድረስ   የምንጠቀምበት ሊሆን ይገባል ሲሉ የገለጹት ደግሞ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ናቸው፡፡

“የሌማት ትሩፋትን ” በከተማዋ ተግባራዊ በማድረግ ሁሉም ዜጋ የለመለመ ማዕድ እና ለጎረቤት የሚተርፍ ገበታ እንዲኖረው የያዝነውን ግብ  ለማሳካት በትጋት መስራት ይኖርብናልም ብለዋል፡፡

በምንተስኖት ሙሉጌታ

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.