Fana: At a Speed of Life!

በሶዌቶ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ አፍሪካ ሶዌቶ በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ርቀቱን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡

በወንዶች ማራቶን ዳባ ኤፋ 42 ኪሎ ሜትሩን 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ በመግባት ቀዳሚ ሲሆን ፥ የሀገሩ ልጅ ጋዲሳ በቀለ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

በሴቶች ማራቶን ጫልቱ በዶ 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ በመግባት በርቀቱ ቀዳሚ መሆን ችላለች፡፡

በዘንድሮው የሶዌቶ ማራቶን ውድድር ከ20 ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች መሳተፋቸወን ስዌቶ ማራቶንን ጠቅሶ አይ ዊትነስ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ ኮሪ ሴኦል በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ  2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ  ከ59 ሴኮንድ በመግባት ቀዳሚ ሆኗል፡፡

አትሌቱ ያስመዘገበው ሰዓት የራሱ የማራቶን ፈጣን ሰዓቱ ሆኑ መመዝገቡን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.