የሀገር ውስጥ ዜና

“ከኢትዮጵያ ጎን እቆማለሁ” በሚል የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ በለንደን እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

November 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከኢትዮጵያ ጎን እቆማለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሰላማዊ ሰልፍ በብሪታኒያ፤ ለንደን በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለፊት እየተካሄደ ነው።

ሰልፈኞቹ “የሰላም ስምምነቱን እንደግፋለን”፣ “አሜሪካ የሰላም ስምምነቱን መደገፏ በበጎ መልኩ እንቀበለዋለን”፣ “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” የሚሉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው።

ሰልፉን ‘ዲፌንድ ኢትዮጵያ ታስክፎርስ ኢሮፕ’ እና በብሪታኒያ የሚገኙ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በጋራ እንዳዘጋጁት ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!