Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከፊፋ ዋና ጸሐፊ ፋትማ ሳሙራን ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉትን የፊፋ ዋና ጸሐፊ ፋትማ ሳሙራን ተቀብለው አነጋገሩ።

ዋና ጸሀፊዋ ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ሁሉ ከ800 በላይ የሚሆኑ አሁን ዓለም እየተጠቀመባቸው ያሉ የመጨረሻ ደረጃ የተለያዩ የእግር ኳስ ትጥቆችን አስረክበዋል።

በተጨማሪም በኳታር በዚህ ዓመት ሕዳር ላይ የሚጀመረው የዓለም ዋንጫ ላይ የሚጠቀሙበትንና የፕሬዝዳንቷን ስም የያዘ ኳስም ነው ያበረከቱት።

ዋና ጸሃፊዋ ድርጅቱ በ90ዎቹ በተከሰተው የዓለም መንግሥታት የአደረጃጀት ማስተካከያ ወቅት ለስፖርትና ለስነዜጋ የትምህርት ዓይነቶች የተሰጠውን አነስተኛ ግምት ለማስተካከል በት/ቤቶች የእግር ኳስ ስፖርትን ለማስፋፋት እየጣረ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቷ በበኩላቸው በኢትዮጵያና በፊፋ መካከል ጠንካራ ግንኙነት ያለ መሆኑን ገልጸው ፥ የእግር ኳስ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ ለሴትና ወንድ ታዳጊ ህጻናት እየተደረገ ላለው ድጋፍ ፊፋን አመስግነዋል።

ከዚህ ቀደምም ፕሬዝዳንቷ ከፊፋ በተገኘ ድጋፍ 600 ለሚጠጉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ትጥቅ ያበረከቱ መሆኑን ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.