Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሩቶ አፍሪካ በዓየር ንብረት ለውጥ ቀደም ሲል የተደረሱ ስምምነቶች በአስቸኳይ እንዲተገበሩ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀደሙት የዓየር ንብረት ለውጥ ስብሰባዎች አፍሪካ በዓየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርስባትን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያስችላት ዘንድ የተደረሱ ስምምነቶች በአስቸኳይ እንዲተገበሩ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጠየቁ፡፡

የኬንያው ፕሬዚዳንት ቀደም ሲል በዓየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አፍሪካ ላይ እየደረሱ ባሉ ተፅዕኖዎች ላይ እንደ አህጉር በቂ ውይይት መደረጉንና በርካታ ቃል-ኪዳኖች መገባታቸውን አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ አፍሪካ ከውይይት እና ከቃላት ባለፈ ሥምምነቶቹ በአስቸኳይ ተግባራዊ የሚሆኑበትን ጊዜ እንደምትሻ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ግብፅ ሻርም ኤል ሸክ እየተካሄደ በሚገኘው 27ኛው የዓየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ ÷ የኬንያውን ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሳሞኢ ሩቶን ጨምሮ ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፣ የኮሞሮሱ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሶማኒ፣ የአንጎላ ምክትል ፕሬዚዳንት ኤስፔራንካ ማሪያ ኤድዋርዶ ፍራንሲስኮ ዳ ኮስታ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.