Fana: At a Speed of Life!

ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማስቀመጫ “ዲቫይሶች”ን ደህንነት እንዴት እንጠብቅ?

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መረጃዎችን ከጥቃት ለመከላከል በተለያዩ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማስቀመጫዎች አማካኝነት መረጃዎችን ሲያስቀምጡ የዲቫይሶችን ወሳኝ የደህንነት ማስጠበቂያ ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

“ዲቫይሶች”ን ከመክፈትዎ በፊት በፀረ- ቫይረስ ስካንማድረግ፣ የግልንና የድርጅትን ዶክመንቶች (ፋይሎች) ለይቶ መመስጠርና ማስቀመጥ፣ እንደ አስፈላጊነቱ በተቋማት ደረጃ ሊከሰት የሚችልን ጉዳት ለመቀነስ የሚጠቀሙበትን ኮምፒውተር ወይም ኤሌክትሮኒክ ዲቫይስ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋቶችን እንዳይቀበል ማድረግን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

እንዲሁም የድርጅትን (የተቋማት)ን የሳይበር ደህንነት የአጠቃቀም ፖሊሲዎችን፣ ስልቶችን፣ ስትራቴጂዎችን መከተል፣ ተንቀሳቃሽ ዲቫይሶችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታና ሁኔታ ማስቀመጥ፣ የመረጃ ማከማቻ ተንቀሳቃሽ ዲቫይሶችን በጠንካራ የይለፍ ቃል መቆለፍ፣ ዲቫይሶችን እርስ በእርስ አለመዋዋስ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማከማቻዎች ደህንነት የማስጠበቂያ ስልቶች ናቸው፡፡

እነዚህን ስልቶች መተግበር በዋናነት የተለያዩ ግላዊ ብሎም ተቋማዊና ሀገራዊ መረጃዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው እንደሚረዳ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህ ማለትም መረጃዎች እንዳይጠፉ፣ አግባብ በሌላቸው አካላት ጥቅም ላይ እንዳይውሉና እናዳይለወጡ በማገዝ መሰረታዊ በሆነ መንገድ የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሚናው የላቀ መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.