የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ ክልል የወባ ስርጭትን መከላከል የሚያስችል ንቅናቄ ተጀመረ

By Feven Bishaw

November 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ኛው ክልል አቀፍ የወባ ሣምንት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

በክልሉ “ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሣምንት በሚቆየው የወባ ሣምንት የተለያዩ ወባን መከላከል በሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከበር ተገልጿል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎ እንዳሉት፥ በክልሉ ባለፉት አምስት ዓመታት የወባ በሽታ እየቀነሰ ቢመጣም በ2014 ዓ.ም ዳግም አገርሽቷል ።

በዚህም በ2014ዓ.ም 101 ሺህ 811 ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን አስረድተው ይህም ከ2013 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር በ64 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ገልፀዋል።

በወባ ሣምንት ንቅናቄው የህብረተሠብ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ወባን መከላከል የሚያስችሉ፥ የምርመራ እና የሕክምና ሥራዎችን ለመስራት ዝግጅት መደረጉን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!