የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ጣሊያን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

By Alemayehu Geremew

November 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የእውቀት ሽግግር ማድረግ ስለሚቻልበት ሁኔታ፣ የልማት ማዕከላትን ስለመገንባት እንዲሁም በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡