Fana: At a Speed of Life!

ሁለቱ ሱዳኖች በአቢዬ ግዛት ጉዳይ ላይ ሊስማሙ መሆኑ ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በአወዛጋቢው የአቢዬ ግዛት ጉዳይ ላይ ለመስማማት ከጫፍ መድረሳቸው ተሰማ፡፡

ሀገራቱ ድንበር ላይ በምትገኘው የአቢዬ ግዛት ሲወዛገቡ እና ሲጋጩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

የአቢዬ ግዛት ጉዳይ ሀገራቱ ከተፈራረሙት የሠላም ሥምምነት ወዲህ የማንኛው ሀገር ግዛት እንደሆነች ሲያወዛግብ እና ጉዳዩ ዕልባት ሳያገኝ እስካሁን ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ ግን አንድ ሳምንት ከፈጀው ከሁለቱ ወገኖች የተውጣጣ ኮሚቴ ውይይት በኋላ ለግዛቷ ዕልባት የሰጠ እና ሁለቱን ወገኖች ያስማማ መፍትሄ ላይ ተደርሷል ነው የተባለው፡፡

በሞሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት እና በደቡብ ሱዳን የጸጥታ አማካሪ ቱት ጋትሉክ ማኒሜ የሚመራ ኮሚቴ፥ በአቢዬ የግዛት ጉዳይ በሰባት ነጥቦች ላይ መስማማታቸውን እና ጊዜያዊ ሪፖርት መቅረቡን ዘ ኢስት አፍሪካን በዘገባው አመላክቷል፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ጸሐፊ ዳፋላህ አል ሃጂ አሊ እንዳስታወቁት ÷ ሁለቱ ወገኖች ዜጎቻቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታም በአግባቡ እንዲደርስ ግብረ-ኃይል ያቋቁማሉ ፣ በመጨረሻም ቀጣይ በውይይት አካሂደው በአቢዬ ግዛት ላይ ዘላቂ እና የማያዳግም መፍትሄ ለመሥጠት ይሰራሉም።

አወዛጋቢዋ የአቢዬ ግዛት በነዳጅ ዘይት የበለጸገች መሆኗ ይነገራል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.