Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ የመፍትሔ አንድ አካል ለመሆን ቁርጠኛ ናት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ እንደምታጋራ እና የመፍትሔ አንድ አካል ለመሆን ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብጽ እየተካሄደ ካለው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ስልታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ከዚህ ባለፈም ከአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋር በጋራ የትኩረት ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ነው የገለጹት።

በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ እንደምትጋራ እና የመፍትሔዎች አንድ አካል ለመሆን ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.