የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

By ዮሐንስ ደርበው

November 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በጥቅምት ወር በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ከጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም በሁለተኛው ምዕራፍ ከመስከረም 18 ቀን 2015 ጀምሮ ዓ.ም ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በሕዳር ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

በዚህም በሕዳር ወር 2015ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም እየተሸጠበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው፡፡

የአውሮፕላን ነዳጅን በተመለከተም በወቅታዊ የዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ በመጣው መሰረት አዲስ አበባ ላይ በሊትር 74 ብር ከ99 ሣንቲም እንዲሸጥ መወሰኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!