የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በአርቲስት ዓሊ ቢራ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

By Mikias Ayele

November 07, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአርቲስት ዓሊ ቢራ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡

አቶ ደመቀ በመልዕክታቸው÷አንጋፋው እና ዝነኛው አርቲስት ዓሊ ቢራ ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ ተወዳጅ ሥራዎቹን በማቅረብ የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር ነበረ ብለዋል።

አቶ ደመቀ ለአርቲስት ዓሊ ቢራ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና አድናቂዎቹ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡