Fana: At a Speed of Life!

በታማኝነት ግብር መክፈል ህጋዊነት ብቻ ሳይሆን ለሀገር እድገት፣ ለዜጎችም ኩራት ነው-ዶ/ር ይልቃል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በታማኝነት ግብር መክፈል ህጋዊነት ብቻ ሳይሆን ለሀገር እድገት፣ ለዜጎች ኩራትና ክብር ጭምር ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷በዛሬው ዕለት ለክልሉ ምስጉን ግብር ከፋዮችና በዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው ዞንና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና መሰጠቱን አንስተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ክልሉ በችግር ውስጥ ሁኖም መስራት እንደምንችል በተጨባጭ አረጋግጠናል ያሉት ዶ/ር ይልቃል ÷ በቀጣይም የተሻለ ለመፈጸም አቅደን መስራት አለብን ብለዋል።

ግብር የሚሰበሰበው የህዝብን ማህበራዊ አገልግሎቶች ለማሟላት፣ ልማትን ለማፋጠንና የጋራ ጠላት የሆነውን ድህነትን በዘላቂነት ለመቅረፍ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በፍትሃዊነትና በተገቢው መንገድ ግብር መሰብሰብ ስንችል ደግሞ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና ኢኮኖሚያችን ማሻሻል እንችላለንም ብለዋል፡፡

ዶ/ር ይልቃል የክልሉ ምስጉን ግብር ከፋዮች ከበፊቱ የተሻለ ለመክፈል፤ዞንና ከተማ አስተዳድሮች ደግሞ ካለፈው ዓመት እጥፍ ለመሰብሰብ አቅደው ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.