Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ወዳጅነት ዐደባባይ ተሸኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ወዳጅነት ዐደባባይ ተሸኘ ፡፡

የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ዛሬ ማለዳ ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሸኘቱ ይታወቃል፡፡

አሁን ደግሞ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ወዳጅነት ዐደባባይ እየተሸኘ ነው፡፡

አርቲስት ዓሊ በአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በ75 ዓመቱ ከትናንት በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡

በወዳጅነት ዐደባባይ የክብር እና የጀግና ስንብት ከተደረገለት በኋላ ወደ ድሬዳዋ አስክሬኑ እንደሚሸኝ ተገልጿል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.