ዓለምአቀፋዊ ዜና

የዌልሱ ልዑል ቻርለስ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

By Tibebu Kebede

March 25, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዌልሱ ልዑል ቻርለስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነገረ።

የ71 አመቱ ልዑል በተደረገላቸው ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸውንና የቫይረሱ ምልክት እንደታየባቸው ከብሪታንያ ንጉሳዊ ቤተሰብ መኖሪያ የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል።

የ72 አመቷ ባለቤታቸው ግን ከቫይረሱ ነጻ ሆነዋል ተብሏል።

አሁን ላይ እርሳቸውና ባለቤታቸው በለይቶ ማቆያ ራሳቸውን አግልለዋልም ነው የተባለው።

በብሪታንያ ከ8 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision