የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በጉባኤው ላይ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንዳሉት ÷ በዚሁ ጊዜ የአፍሪካ ኢንጂነሪንግ ጉባኤ የአህጉሪቱን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ከፍ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ ነው፡፡
በአፍሪካ ምቹና ተስማሚ የግንባታ ስራዎችን ለማከናወን እንደሚያግዝ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።