የሀገር ውስጥ ዜና

በርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የተመራ ልዑክ በአሶሳ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎበኘ

By Shambel Mihret

November 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በአሶሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በግብርና ምርምር ማዕከሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የሠብል እና የእንስሳት ልማት ስራዎችን  መመልከታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።