Fana: At a Speed of Life!

ዓሊ ቢራን ማጣት የሚያሳዝን ቢሆንም ሥራዎቹንና ራዕዩን የማስቀጠል አደራ አለብን – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓሊ ቢራን ማጣት የሚያሳዝን ቢሆንም ሥራዎቹንና ራዕዩን የማስቀጠል አደራ አለብን ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

በትውልድ ሥፍራው ድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የአርቲስት ዓሊ ቢራ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ስርዓት ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ፥ ዓሊ ቢራ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ኩራት እንደነበር አንስተዋል፡፡

በዚህም÷ አርቲስት ዓሊ ቢራ ዘመን የማይሽራቸውን በርካታ ሥራዎች አበርክቶልናል ፤ ከእነዚህ ሥራዎቹም ብዙ ተምረናል ብለዋል፡፡

በተለይም በብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት፣ በአብሮነት፣ በወንድማማችነት እንደ ሐረሪ ክልል መንግስት ላበረከተው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ክብር አለን ነው ያሉት፡፡

ሞት ለማንም አይቀርም ፤ ትልቁ ነገር የማይረሳ አሻራ ጥሎ ማለፍ ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ዓሊ ቢራን ማጣት የሚያሳዝን ቢሆንም ሥራዎቹንና ራዕዩን ማስቀጠል አደራ አለብን ብለዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ዓሊ ቢራ ስለሀገር ፍቅርና ስለህዝብ ፍቅር በርካታ ሥራዎችን ሰርቶ ማለፉን ያነሱት አቶ አርዲን ፥ እነዚህ ሥራችን ማስቀጠል ከሁላችን ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ፥ ለቤተሰቦቻቸውና ለአድናቂዎቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

በመሰረት አወቀ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.