አቶ አወል አርባ በሰብዓዊ እርዳታ ላይ በኢትዮጵያ ከጀርመን ምክትል አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኢትዮጵያ ከጀርመን ምክትል አምባሳደር ሄይኮ ኒትስሽክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ጀርመን በአፋር ክልል ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ማድረግ በምትችልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
አቶ አወል አርባ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷በወቅታዊ የሰብዓዊ ሁኔታ፣ በቀጣናው የልማት ጉዳዮች እና የሰላም ስምምነቱ አተገባበር ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
የጀርመን መንግሥት በአፋር ክልል ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡