የጋምቤል ክልል ለሰላም ስምምነቱ ገቢራዊነት በቁርጠኝነት ይሰራል – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤል ክልል ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ፡፡
የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሰላም ስምምነቱ መሰረታዊ ጭብጦች እና ተግባራዊነት ዙሪያ የተዘጋጀ ማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በፌዴራል መንግስትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ÷ በፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ እንዲሆን የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።
አቶ ኡሞድ የሰላም ስምምነቱ መልካም ቢሆንም ተግባራዊነቱ ግን ከፍተኛ ትዕግስትና ፅናትን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን ነው በአጽንኦት የገለጹት፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን÷በቀጣይም በሰላም ስምምነቱ ዙሪያ ውይይት ይካሄዳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!