ቢዝነስ

ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

By Alemayehu Geremew

November 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ፋሃድ አልሁማይዳኒ ጋር ተወያዩ።

በውውይታቸው ወቅት በሀገራቱ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ዙሪያ መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በዚህ ወቅትም የሀገራቱን የንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት ለማጠናከር መስማማታቸውን ጠቁመዋል።