የሀገር ውስጥ ዜና

በሐረሪ ክልል የ2015 በጀት ዓመት የበጋ መስኖ ልማት ሥራ በይፋ ተጀመረ

By Feven Bishaw

November 09, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ሁለተኛው ዙር የ2015 በጀት ዓመት የበጋ መስኖ ልማት ሥራ በይፋ ተጀምሯል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሚስራ አብደላ እንደገለጹት÷ በክልሉ በ2015 በጀት ዓመት ከ4 ሺህ ሔክታር በላይ በበጋ መስኖ ልማት ይለማል፡፡

በመስኖ ከሚለማው መካከል 150 ሔክታር ያህሉ በስንዴ ይሸፈናል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

አርሶ አደሩ በሚያከናውናቸው የበጋ መስኖ ልማት ሥራዎች ምርትና ምርታማነት እንዲጎለብት ለማስቻል የግብዓት አቅርቦትና ሌሎች ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!