Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ የመረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ ኃላፊ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጀነራል ማሀድ ሞሐመድ የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ መግባቱን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ልዑኩ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው የሀገሪቱን የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች፣ በአቅም ግንባታ መስኮች እንዲሁም ቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በሚደረጉ የጋራ ስምሪቶች ዙሪያ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራሮች ጋራ ምክክር እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

በቅርቡ በኢትዮጵያ በኩል ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከመከላከያ ሠራዊት እና ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የተውጣጣ ልዑክ በሶማሊያ በአልሻባብ ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው ሶማሊያውያን የሚውሉ የተለያዩ የሕክምና መሣሪያዎችና መድሐኒቶችን በሀገሪቱ በመገኘት ድጋፍ ማድረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የላከልን መረጃ አስታውሷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.