የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ አገልግሎት መጀመሩ እፎይታ ሰጥቶናል- የጥሙጋ እና አላማጣ ነዋሪዎች

By ዮሐንስ ደርበው

November 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ አገልግሎት መጀመሩ እፎይታ ሰጥቶናል ሲሉ የጥሙጋ እና አላማጣ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ÷ በጥሙጋ የኤሌክትሪክ እና የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በኢፌዲሪ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መካሄዱ እና ስምምነቱን ተከትሎም አገልግሎት በመጀመሩ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከኤሌክትርክ እና የሞባይል ኔትወርክ በተጨማሪ ሌሎች አገልግሎቶችም እንዲጀመሩ እና የሰብዓዊ ድጋፉንም በፍጥነት የማዳረስ ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በሐይማኖት ወንድራድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!