የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ልዩ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

By Shambel Mihret

November 10, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1ኛ ልዩ ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

በጉባዔው የክልል ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን÷ የምክር ቤቱ የ100 ቀን እቅድ እና ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ማድረግም በጉባዔው ከተያዙ አጀንዳዎች መካከል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-