Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የ18 ቢሊየን ዶላር ብድር ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የ18 ቢሊየን ዶላር የረጅም ጊዜ ብድር ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል፡፡

የህብረቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ቫልዲስ ዶምብሮቭስኪስ እንደገለፁት÷ የአውሮፓህብረት ለዩክሬን ለመስጠት ያቀደው ብድር በ35 ዓመታት ውስጥ የሚመለስ ነው፡፡

ህብረቱ ገንዘቡን ከዓለም አቀፍ ገበያ በመበደር  ለዩክሬን የሚሰጥ  ሲሆን÷ የብድሩ ወለድም በህብረቱ የሚሸፈን መሆኑን  ገልፀዋል፡፡

ከሩሲያ – ዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞ  ኪዬቭ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋታል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ÷ የህብረቱ  ሀገራት ብድሩን በዓመቱ መጨረሻ ላይ እንዲያጸድቁት ጠይቀዋል፡፡

ብድሩን ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ይሁንታ የሚያስፈልግ ሲሆን÷ ሀንጋሪ በገንዘብ ብድሩ ላይ አለመፈረሟ ተመላክቷል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ቃል ከገባው 9 ቢሊየን ዶላር ብድር ውስጥ  4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላሩን የሰጠ ሲሆን÷ 2 ቢሊየን ዶላሩ ደግሞ ለኪዬቭ ወታደራዊ ድጋፍ መዋሉን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.