Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከቱርክ ኤምባሲ የንግድ ኮንሶላር ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሚሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከቱርክ ኤምባሲ የንግድ ኮንሶላር ከሆኑት ጣሀ አልፕሬን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች እንዲሁም ከቱርክ ኤምባሲ ጋር ኮሚሽኑ በጋራ መስራት በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በምክክሩ የንግድ ኮንሶላር ጣሀ÷ የሁለቱን ሀገራት የኢንቨስትመንት እና የንግድ ግንኙነት በማጠናከር የቱርክ ባለሀብቶችን ወደ ኢትዮጵያ በመሳብ በኢንቨትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.