Fana: At a Speed of Life!

የሥራ አጥነት ችግርን ለመፍታት የምክር ቤቱ አባላት ቅንጅታዊ ሥራ አስፈላጊ ነው- ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ አጥነት ችግርን ለመፍታት የምክር ቤቱ አባላት ቅንጅታዊ ሥራ አስፈላጊ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከወረዳ እስከ ማዕከል ከሚገኙ የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት አባላት ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ እና ምክትል ከንቲባና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ተገኝተዋል፡፡

ወይዘሮ አዳነች እንደገለጹት÷ የከተማዋን የሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት የምክር ቤቱ አባላት ቅንጅታዊ ሥራ አስፈላጊ ነው፡፡

የሥራ ዕድልና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ ፍስሃ ጥበቡ የሥራ ዕድል ፈጠራ የንቅናቄ ዕቅድና ነባራዊ ሁኔታን የተመለከተ ሰነድ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡

በ2015 በጀት ዓመት በ4 ወር ከ15 ቀን ውስጥ÷ ለ55 ሺህ 504 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ በሰነዱ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.