Fana: At a Speed of Life!

ተቋማት ለጥቃት እንዳይጋለጡ የሳይበር ደኅንነት መጠበቅ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይበር ደኅንነት ወር መከበር መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሳይበር ደኅንነት ተጋላጭነታቸውን እንዲለዩና እንዲቀንሱ ለማድረግ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ገለጸ፡፡

ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው 3ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ማጠቃለያ ዙሪያ መግለጫ ተሰጥቷል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባለፈው አንድ ወር ሲያካሂድ በቆየው የሳይበር ወር የተከናወኑ ተግባራት በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ወሩ የሳይበር ደህንነትን ተጋላጭነት መቀነስ፣ በሳይበር ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ሚናቸው እንዲጨምር ማድረግ ፣ በዘርፉ የሚታየውን የሰው ሀብት ውስንነት ማጠናከር፣ ማህበረሰብ አቀፍ ንቃተ ህሊናን የመጨመር አላማዎችን ይዞ መከበሩን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡

የግሉን ዘርፍ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር እንዲገናኑ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ወር እንደነበርም አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

የሳይበር ወር በወርሃ ጥቅምት የሳይበር ደህንነት ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሐ ግብር ሲሆን ወሩ በኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ ነው የተከበረው።

በፍቅርተ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.