Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በፎገራ ወረዳ የለማ የሩዝ ማሳን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ በአርሶ አደሮች የለማ የሩዝ ማሳን ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የፎገራ ሩዝ ሰብል ቁመና በምግብ ራሳን ለመቻል አበረታች ውጤት የታየበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አርሶ አደሮች ምርታማነትን የሚያሳድግ አዳዲስ የቴክኖሎጅ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ማድረግ እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡

የክልሉ መንግስት የፎገራ ወረዳን ጨምሮ በኩታ ገጠም እርሻ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች የምርት መሰብሰቢያ ማሽን ለማቅረብ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በክልሉ በሁሉም አካባቢ የታየው የሰብል ልማት ቁመና እንደሀገር ያለውን የምግብ ክፍተት ለመሙላት ትልቅ አቅም እንደሚሆን ጠቁመው÷ የ ግብርናው ዘርፍ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.