Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ቤት ምገባ መዝጊያ እና አዲስ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉን አቀፍ ሀገር በቀልና አካታች የትምህርት ቤት ምገባ መዝጊያ እና አዲስ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ግሎባል ፓርትነር ሺፕ ፎር ኤጁኬሽን (ጂፒኢ) ከትምህርት ሚኒስቴር ፣ ከዓለም አቀፉ ህፃናት አድን ድርጅት እና ከክልልላዊ አጋር ተቋማት ጋር በመሆን ሲተገብር የቆየው ሁሉን አቀፍ ሀገር በቀልና አካታች የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ፕሮጀክት በስኬት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ ከፈረንጆቹ ታህሳስ 1 ቀን 2020 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2022 ድረስ ሲተገበር መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡

ፕሮጀክቱ 223 ሺህ 301 ህፃናትን በትምህርት ቤት ምገባ የደገፈ ሲሆን በትምህርት ቤት ምገባ እና በሎሎች የፕሮጀክት ተግባራት አማካኝነት በአጠቃላይ 648 ትምህርት ቤቶችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች ተዛማጅ ድጋፎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ ለታዳጊ ሴት ተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎችን በፕሮጀክቱ ለታቀፉ ትምህርት ቤቶች ተደራሽ ማድረጉም ተገልጿል።

በሁሉን አቀፍ ሀገር በቀልና አካታች የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ፕሮጀክት በተገኙ ስኬቶች የተደሰተው ግሎባል ፓርትነር ሺፕ ፎር ኤጁኬሽን በስድስት ክልሎች በተመረጡ 578 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት እና ሌሎች ተያያዥ ድጋፎችን ለማስቀጠል የሚያስችል ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አፅድቋል።

አዲሱ ፕሮጀክት ከፈረንጆቹ ሕዳር 1 ቀን 2022 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 31 ቀን 2023 እንደሚቆይ ተገልጿል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.