የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ትናንት የተከፈተውን ዓለም አቀፍ ማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ጎበኙ

By Tamrat Bishaw

November 11, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት የተከፈተውን ዓለም አቀፍ ማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ጎበኙ።

ኤክስፖው ትናንት ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ መከፈቱ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ባለው በዚህ ኤክስፖ ከ270 በላይ ኩባንያዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

ኤክስፖው የኢትዮጵያን የማዕድን ሃብት በማስተዋወቅ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።