የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል።
በውይይቱ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን፣ የብልፅግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ፅህፈት ቤት ሀላፊ መሀመድ ሻሌና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ውይይቱ የኢፌዴሪ መንግስት ከሕወሓት ጋር የደረሠው የሠላም ስምምነት ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው ተገለፀው፡፡
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ መሀመድ ሻሌ በደቡብ አፍሪካ የተደረሰውን ስምምነት በተመለከተ አመራሩ በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ ለተግባራዊነቱ የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ዑስማን በበኩላቸው አመራሩ የሀገሪቱን በተለይ የክልሉን ኢኮኖሚ ከፍ ለማድረግ የተጀመረው የግብርና ልማት ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ማለታቸውን የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡